Call for Application

ትምህርት ሚኒስቴር እና ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና ከእንግሊዝ የውጭ የጋራ ልማት ቢሮ (FCDO) ጋር በመተባበር ዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር (University Industry Linkage) ላይ ያተኮሩ ችግር ፈቺ የምርምር ውጤት ያላቸውን ተመራማሪዎች ወይም የፈጠራ ባለቤቶች በማወዳደር ወደ ገበያ እንዲገቡ የፋይናንስ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም በዩኒቨርሲቲዎች፣ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት፣ በምርምር ተቋማት እንዲሁም በኢንዱስትሪ ተጠናቀው ወደ ምርትና አገልግሎት ሊቀየሩ የሚችሉ እና ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት አስተዋፆ የሚያበረክቱ የምርምር ውጤቶች ያላችሁ ተመራማሪዎች እና የፈጠራ ባለሙያዎች ከዚህ በታች የተቀመጠውን ቅጽ በመጠቀም እስከ የካቲት 11 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንድታመለክቱ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
https://docs.google.com/forms/d/1xE-l63ZDhFrtMqDuYGwzncbFgDk1xQ8Vj96ZKcOTw8U/edit?ts=63bfce75 

ለበለጠ መረጃ ፡ 0948 862349 ወይም 0912 612679 ይደውሉ፡፡